በትምህርቱ ዘርፉ ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባል - ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

  በትምህርቱ ዘርፉ ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባል - ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ 

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትምህርቱ ዘርፍ የሚደረገውን ኢንቨስትመንት ማሳደግ እንደሚገባ ገለጹ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሪ አዙላይ ባዘጋጁት የዓለም አቀፉ የትምህርት ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቷ በበይነ መረብ አማካኝነት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንዳነሱት ÷ በትምህርት ዘርፉ ላይ ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም ፕሬዚዳንቷ እንደ ዓለም አቀፍ የትምህርት ኮሚሽን ሰብሳቢነታቸው በወደፊቱ የትምህርት ዘርፍ የመላው ሴቶችን በተለይም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ሰለባ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ተጠቃሚነት አኳያ ጥረት እንደሚያደርጉም ነው የገለጹት።

ፕሬዚዳንቷ የኮሚሽኑ አባላት ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደረጉ 19 ስብሰባዎች ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል።

አያይዘውም የተመድ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በሰዎች አዕምሮ ውስጥ ሰላምን የመገንባት ሃላፊነት አለበት ማለታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፕሬዚዳንቷ በንግግራቸው የሰላም ባህል እንዲዳብር እና ትምህርትን ለሰላም ማዋል በሚቻልበት አግባብ ላይ መስራት ይገባልም ብለዋል።

ትምህርትም ከዚህ አንጻር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።


ምንጭ- FBC




Post a Comment

Previous Post Next Post